የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሌየም አክሲዮን ማህበር 

                                                                              

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ

የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 15ኛ መደበኛ እና 7ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ  ህዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 08፡00 ሰዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል፡፡

ስለሆነም የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ተወካዮቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ቦታና ሰዓት በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

      የባለአክሱዮኖች 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ

1.የ2018/19 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድን የስራ ክንውን ሪፖርት ማዳመጥ፣

2.  የ2018/19 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ፣

3.  ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

4.  በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል/አከፋፈል ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

5.  የ2019/20 በጀት ዓመት የወጪ ኦዲተሮችን መምረጥና ክፍያውን መወሰን፣

6.  የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ፡፡ 

     የባለአክሲዮኖች 7ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ

1.  አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፣ የተደረጉ የአክሲዮን ግዢ እና ዝውውሮችን እንዲሁም በውርስ የተላለፋ አክሲዮኖችን ማሳወቅ፣

2.  በኩባንያው መተዳደሪያ ደንብ እና መመስረቻ ጽሁፍ ላይ መወያየት፣

3.  የእለቱን ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፡፡

    ማሳሰቢያ፡-

1.  በጉባኤው ላይ ለመገኘት የማይችሉ ከሆነ ሌላ ሰው መወከል የሚችሉ ሲሆን ውክልናውም፡-

ሀ. ከሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ጽ/ቤት የተረጋገጠ ወይንም፣

ለ. ጉባኤው ከመደረጉ ሶስት /3/ ቀን በፊት ባለአክሲዮኑ ራሣቸው በአካል ቀርበው ከማህበሩ የውስጥ ኦዲተር ፊት በመፈረም በሰነድ የተረጋገጠ ውክልና በመስጠት መሆን ይኖርበታል፡፡

2.  ውክልና ለመስጠትም ሆነ በጉባኤው ለመሣተፍ የሚመጡ ሁሉም ባለአክሲዮኖች ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም መንጃ ፈቃድ ወይንም ፓስፖርት መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ